Share on LinkedInShare on LinkedIn

ARTICLE · 03 MARCH 2026

የአስገዳጅ የህግ ትርጉም "ፓራዶክስ"፦ የዳኝነት ነክ ሥልጣን የተሰጣቸው አካላት የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰ/ሰ/ችሎት አስገዳጅ የህግ ትርጉም ያስገድዳቸዋልን?

1.1. ፍትሐዊ እና ሥርዓት ያለው ማኅበረሰብን ለመገንባት በሚደረግ ጥረት ውስጥ የህግ ወጥ አፈጻጸም እንደ መሠረታዊ መርህ የሚታይለት ነገር ጥቂት

EthiopiaLitigation, Mediation & Arbitration

1. መግቢያ

1.1. ፍትሐዊ እና ሥርዓት ያለው ማኅበረሰብን ለመገንባት በሚደረግ ጥረት ውስጥ የህግ ወጥ አፈጻጸም እንደ መሠረታዊ መርህ የሚታይለት ነገር ጥቂት ነው፡፡ አንድ የህግ ሥርዓት ወጥነት ባለውና በተናበበ መንገድ ሲፈፀም ተገማችነትን ያሰፍናል፣ እኩልነትን ያረጋግጣል፣ የህግ የበላይነትንም ያጠናክራል ተብሎ ይታመናል፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (ኢ.ፌ.ዲ.ሪ) በህገ-መንግስታዊ ቅርፅ እና ይዘቱ ይህንን ወጥነት የማረጋገጥ የመጨረሻውን ኃላፊነት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠ ሲሆን፣ የሰበር ሰሚ ችሎቱ በማንኛውም የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ ላይ የሚገኝን "መሠረታዊ የህግ ስህተት" እንዲያርም ሥልጣን ሰጥቶታል።

1.2. ይህ አሠራር በንድፈ-ሀሳብ ደረጃ የሀገሪቱን የዳኝነት ሥርዓት እንደ ምርኩዝ ሆኖ የሚያገለግልና ከሀገ መንግስት ትርጉም በመለስ ባሉት የሌሎች ህጎች ትርጉም አሳማኝነት በሌላቸው በተለያዩ ምክንያቶች በተለያዩ ተቋማዊ ወይም አካባቢያዊ ዘዬዎች የተዘበራረቀ እንዳይሆን የማድረግ ኃይል ይኖረዋል ተብሎ የሚታመን ነው፡፡ ህግ መንግስቱ ሲረቀቅ የነበሩት ውይይት ሰነዶች የሚመስክሩትም ይህንኑ ነው፡፡ ይህንን ህገ-መንግስታዊ ርይዕ ወደ ተግባር ለመለወጥ ቀድሞ የወጣው አዋጅ ቁጥር 454/1997'ም' ሆነ ይህንኑ አዋጅም ሆነ ሌሎች ተያያዥ አዋጆችን በመተካት ስራ ላይ ያለው የፌ/ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፪፻፴፬/፪ሺ፲፫ አስገዳጅነት ያለው የህግ ትርጉም ሥርዓትን ዓላማና ግብ ምን እንደሆነ በግልፅ ያስቀመጠ ይፋዊ የህግ አውጪ ሀሳብ የሚያሳይ ድንጋጌ ባይዝም ስርዓቱን ቀደሞ

We operate a free-to-view policy, asking only that you register in order to read all of our content. Please login or register to view the rest of this article.

See more popular content from