ሰበር አጣሪ
ችሎት፦የባለ5ቱ
ዳኞች ሰበር ችሎት
"በር ጠባቂው"
ችሎት
የፌ/ ጠ/ፍ/ቤት
ሰበር አጣሪ ችሎት
የሰበር አቤቱታን
በቃል የሚሰማበት
ሂደት ሕጉና
አሠራሩ
1.1. የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ
መንግስት
ለፌ.ጠ.ፍ.ሰ.ች
በሀገሪቱ
የዳኝነት ሥርዓት
መዋቅር ውስጥ ልዩ
እና ወሳኝ ቦታ
ማስያዙ
ይታወቃል።
በሕገ-መንግሥቱ
የተቋቋመው የዚህ
ችሎት ዋነኛ
ሥልጣን እንደ
ሦስተኛ ደረጃ
የይግባኝ ሰሚ
ችሎት ሆኖ
ማንኛውንም
ስህተት ማረም
ሳይሆን ከሥር
ፍርድ ቤቶች
በተሰጡ የመጨረሻ
ውሳኔዎች ላይ
የተፈጸሙ
"መሠረታዊ የሕግ
ስህተቶችን"
ማረም ነው። ይህ
ሥልጣን በመላ
ሀገሪቱ ወጥ የሆነ
የሕግ ትርጉምና
አተገባበር
እንዲሰፍን
ለማድረግ ቁልፍ
ሚና ይጫወታል።
የሰበር ችሎቱ
መሰረታዊ የሆኑ
የህግ ስህተት
ያለባቸውን
የመጨረሻ
ውሳኔዎችን
ለማረም
የሚያስችለውን
ህገ መንግስታዊ
ስልጣኑን ዝርዝር
ስርዓት
በተመለከተ
በዝርዝር ህግ
ሊወሰን
እንደሚገባ ህገ
መንግስቱ ራሱ
በደነገገው
አግባብና በሌሎች
አገራት
እንደተለመደው
የሰበር ችሎቱ
የራሱ የሆነ
የችሎት
አደራጃጀትና ስነ
ስርዓት
እንዲኖረው
ተደርጎ ሲሰራበት
እንደቆየና አሁን
ባለው የህግ
ማዕቀፍም ችሎት
ይህንኑ አሰራር
በተወሰነ መልኩ
በማሻሻል
አጠናክሮ መቀጠሉ
ይታወቃል፡፡
አሁን ባለው
የፌዴራል ፍርድ
ቤቶች አዋጅ ቁጥር
1234/2013 የሰበር
አቤቱታዎችን
ለማጣራት
የሚያስችል
ሥርዓት
ተዘርግቷል። ይህ
አዋጅ "የሰበር
አጣሪ ችሎት"
በመባል
የሚታወቀውንና
በሦስት ዳኞች
የሚዋቀረውን
ችሎት በማቋቋም
ወደ ባለአምስቱ
የሰበር ችሎት
የሚቀርቡ
አቤቱታዎችን
አስቀድሞ
በማጣራት "የበር
ጠባቂነት"