Share on LinkedInShare on LinkedIn

ARTICLE · 04 MARCH 2026

ከሰባት ያላነሱ ዳኞች የሚሰየሙበት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሕግ ትርጓሜን የመለወጥ ሥልጣንና አንድምታው፦ የሰበር መዝገብ ቁጥር 242314 ማህበረ-ህጋዊ ዳሰሳ

የአንድ ሀገር የመጨረሻ ዳኝነት ሰጪ አካል የራሱን አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ የመሻር ሥልጣኑ እጅግ ጥንቃቄ የሚጠይቅ ቢሆንም የዳኝነት ነፃነትǛ

EthiopiaGovernment, Public Sector

1, መግቢያ ባጭሩ

የአንድ ሀገር የመጨረሻ ዳኝነት ሰጪ አካል የራሱን አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ የመሻር ሥልጣኑ እጅግ ጥንቃቄ የሚጠይቅ ቢሆንም የዳኝነት ነፃነትና የሕግ ዝግመተ ለውጥ ወሳኝ መገለጫ ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ ሥልጣን በሁለት የሕግ የበላይነት መሠረታዊ መርሆዎች መካከል ያለውን ሚዛን ለመጠበቅ የሚያገልግል ወሳኝ የዳኝነት መሳሪያት ነው፡፡ እነርሱም በአንድ በኩል የሕግ መረጋጋትና ተገማችነት (Legal stability and predictability/Certainty) እና በሌላ በኩል ደግሞ ሕግ ተለዋዋጭ ፍትሕን የማረጋገጥ (Flexibility for Justice) ግዴታ ናቸው። በመሆኑም አንድን አስገዳጅ ትርጓሜ የመሻር ውሳኔ ቀላል የአቋም ለውጥ ሳይሆን የቀደመውን የፍርድ ውሳኔ ሕጋዊ ተፈጻሚነት የሚቀር ሃይል ያለው በመሆኑ ጥልቅ የዳኝነት ተግባር ነው። ይህ ጥልቅ የዳኝነት ተግባር በዋናነት በሚከተሉት መሠረታዊ ምክንያቶች ይደገፋል፡፡ የመጀመሪያው ስህተትን ማረም ሲሆን፣ በዚህም ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል የሰጠው ውሳኔ/ትርጓሜ በተሳሳተ አመክንዮ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ሲገነዘብ ታሪካዊ ስህተቱን ያስተካክላል፡፡ ሁለተኛው ህግን ከዘመኑ ጋር ማጣጣም ነው፡፡ ይህም ህጉ ከአገራዊ ወይም ዓለም አቀፋዊ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦች ጋር አብሮ የሚራመድ ህያው ሰነድ እንዲሆ ያስችለዋል ተብሎ በብዙሃኑ የዘርፉ ምሁራን ይታመናል፡፡ ሶስተኛው ደግሞ የአስተምህሮ ውህደት ሲሆን በዚህም ፍርድ ቤቱ በራሱ ውሳኔዎች መካከል የተፈጠረን ተቃርኖ በማስወገድ የህግ ወጥነትን ለማረጋገጥ ያስችለዋል የሚለው ስለመሆኑ የምርምር

We operate a free-to-view policy, asking only that you register in order to read all of our content. Please login or register to view the rest of this article.

See more popular content from